Dean Message

የደ/ብርሃን ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ቀደም ሲል የደ/ብርሃን መለሰተኛ ጤና ባለሙያዎች  ማሠልጠኛ ት/ቤት  ተብሎ በ1991 ዓ.ም  በ4 መምህራንና በ2ዐ ድጋፍ ሰጭ ሰራተኞች 2ዐ ግንባር ቀደም ጤና ባለሙያዎችን በማሠልጠን ስራውን የጀመረ  ሲሆን   በክልላችን በየደረጃው የሚያስፈልገውን የሰለጠነ የሰው ኃይል ፍላጐት ለማሟላት የመለስተኛ ጤና ሙያ ስልጠና መርሃ ግብር ወደ መካከለኛ ደረጃ ጤና ባለሙያ ማሠልጠኛ ተቋማት ከማስፋፋት ጎን ለጎን የስልጠናውን ቀጣይነት ይበልጥ ማጎልበት ተገቢ መሆኑ ስለታመነበት በክልሉ ውስጥ በመካከለኛ ደረጃ በጤና ሙያ የሰለጠነ የሰው ኃይል ፍላገትን ለማሟላት በሽታን በመከላከል ላይ ያተኮረውን የጤና ፖሊሲ ተግባራዊ ማድረግና መንግስት በሁሉም መስኮች የቀየሳቸውን የልማት ስትራቴጂዎች በሚገባ ማስፈፀም በማስፈለጉ በ1997 ዓ.ም ወደ ኮሌጅ ደረጃ በማደግ በአሁኑ ሰዓት በ9 የተለያዩ የትምህርት አይነቶች ማለትም በነርስ ፣ በሚድዋይፍሪይ ፣ በፋርማሲ ቴክኒሽያን፣ በጤና መረጃ ቴክኒሽያን፣ በጤና ኤክስቴንሽን፣ በላብራቶሪ ፣ አንስቴዥያ፣ ኢመርጀንሲና ጀነሪክ ጤና ኤክስቴንሽን  በመደበኛና በክረምት ትምህርት እየሰጠ ሲሆን እነዚህን ተማሪዎች ለማሰተማርም 34 መምህራንና 36 የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ያሉት ሲሆን ወደፊትም በተለያዩ የትምህርት አይነቶች የክልሉን የስልጠና ፍላጎት በተከተለ ለማሰልጠን የተዘጋጀንና ውጤቱንም በሰራዊት አግባ ለመፈፀም ቆርጠን የተነሳን ሲሆን የትምህርት ጥራትን ለመጠበቅ የኮሌጁ መምህራን እና ሰራተኞች ባሳዩት ቁርጠኝነት የተገኘውን አኩሪ ውጤት በብቃት ምዘናም የተረጋገጠ መሆኑን ስንገልፅ ከልብ የመነጨ ደስታ የሚሰማኝና ለውጤቱ ስኬት የአጋሮቻችንን ታላቅ ሚና እና አስተዋጽኦ ጭምር በመሆኑ ላቅ ያለ አክብሮቴን እየገለፅኩ ለወደፊትም ጥረቶቻችሁን በበለጠ አጠናክራችሁ ከጎናችን እንድትሰለፉና የበኩላችሁን እንድትወጡ መልዕክቴን አስተላልፋለሁ፡፡

ማሙዬ መንገሻ

የኮሌጁ ዲን

Federal Ministry of Health

የፌደራል ጤና ጥበቃ ቢሮ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግና የሕብረተሰቡን የጤና ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ ለማሻሻል ከ21 ጤና ሣይንስ ኮሌጆች ጋር በቅንጅት በመስራት ብቁ የጤና ባለሙያዎችን እንዲያፈሩ፤ ለህብረተሰቡ ችግር ፊቺ የሆኑ ጥናትና ምርምርና የማህበረሰብ የጤና አገልግሎት እንዲሰጡ በተለያየ መልኩ ድጋፍ በማድረግና በቅንጅት በመስራት ሀገራዊ የጤና ተልእኮን ለማሳካት ከጤና ሣይንስ ኮሌጆች ጋር እየሰራ ይገኛል፡፡ more...

Amhara regional health bureau

የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግና የሕብረተሰቡን  የጤና ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ በማሻሻል ረገድ ከጤና ሣይንስ ኮሌጅ ጋር በቅንጅት በመስራት ርህሩህ፣ተገልጋይ አክባሪ እና ሙያዊ ስነ ምግባር የተላበሱ የጤና አገልግሎት ሰጪዎች የማፍራት ስራ፤ ለህብረተሰቡ ችግር ፊቺ የሆኑ ጥናትና ምርምርና የማህበረሰብ የጤና አገልግሎት በመስጠት ከጤና ኮሌጁ ጋር በቅንጅት በመስራት ሀገራዊ የጤና ተልእኮን ለማሳካት በጋራ ከጤና ሣይንስ ኮሌጅ ጋር እየሰራ ይገኛል፡፡ more...