የኮሌጁ ራዕይ /Vision/

የመማር ማስተማር ደረጃውን ከመካከለኛ ጤና ባለሙያዎች ሥልጠና ወደ ከፍተኛ ደረጃ አድጐ ከፍተኛ የጤና ባለሙያዎች የሚፈሩበት እንዲሁም ጤና ነክ ጥናትና ምርምር የሚካሄድበት ማዕከል ሆኖ ማየት፡፡

የኮሌጁ ተልዕኮ /Mission/

በክልሉ ውስጥ በሽታዎችንና  አደጋዎችን  ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል  ስልትን  በመንደፍ  የህብረተሰቡን የጤና ችግር መቅረፍ የሚችሉ፣የጋራ አሰራርን የሚከተሉ፣ብቃት ያላቸው በሙያ ስነምግባር የታነፁ የመካከለኛ ደረጃ የጤና ባለሙያዎችን ማፍራት፡፡

የደ/ብርሃን ጤና ሣይንስ ኮሌጅ አመሠራረት እና ታሪካዊ አመጣጡ ከዛሬ 14 ዓመት በፊት በሰሜን ሸዋ ዞን ከደ/ብርሃን ከተማ 17 ኪሎ ሜትር ርቀት አካባቢ የምትገኝ ጐሸባዶ ቀበሌ ገ/ማህበር ውስጥ አንድ ሬድባርና የተባለ ግብረሰናይ ድርጅት የራሱን ተልዕኮ ይዞ ይንቀሳቀስ እንደነበር አንዳንድ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ድርጅቱ የራሱን ኘሮጄክት ከጨረሰ በኋላ ለቢሮ ያዘጋጀውን የአማረና የተዋበ ሕንፃ ለሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ ከነሙሉ ማቴሪያሉ አስረክቦ ነበር ወደመጣበት የተመለሰው ይህ በእንዲህ እንዳለ የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ በክልሉ የሚገኙ ተመላሽ ሠራዊትን ለማጠናከርና አቅማቸውን አጐልብቶ ወደ ሕብረተሰቡ ለማቀላቀል አቅዶ በጤናው ዘርፍ በመከላከያ ሠራዊቱ ውስጥ የመጀመሪያ ሕክምና እርዳታ ሲሰጡ የነበሩ ነገር ግን ምንም ሠርተፊኬት የሌላቸውን መርጦ እነዚህን አካላት ሠርቲፋይድ ለማድረግ አስቦ ለዚህም ስኬት የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊነት ተሰጥቶት ሥራ እንዲጀምር ሲደረግ ነበር፡፡

Federal Ministry of Health

የፌደራል ጤና ጥበቃ ቢሮ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግና የሕብረተሰቡን የጤና ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ ለማሻሻል ከ21 ጤና ሣይንስ ኮሌጆች ጋር በቅንጅት በመስራት ብቁ የጤና ባለሙያዎችን እንዲያፈሩ፤ ለህብረተሰቡ ችግር ፊቺ የሆኑ ጥናትና ምርምርና የማህበረሰብ የጤና አገልግሎት እንዲሰጡ በተለያየ መልኩ ድጋፍ በማድረግና በቅንጅት በመስራት ሀገራዊ የጤና ተልእኮን ለማሳካት ከጤና ሣይንስ ኮሌጆች ጋር እየሰራ ይገኛል፡፡ more...

Amhara regional health bureau

የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግና የሕብረተሰቡን  የጤና ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ በማሻሻል ረገድ ከጤና ሣይንስ ኮሌጅ ጋር በቅንጅት በመስራት ርህሩህ፣ተገልጋይ አክባሪ እና ሙያዊ ስነ ምግባር የተላበሱ የጤና አገልግሎት ሰጪዎች የማፍራት ስራ፤ ለህብረተሰቡ ችግር ፊቺ የሆኑ ጥናትና ምርምርና የማህበረሰብ የጤና አገልግሎት በመስጠት ከጤና ኮሌጁ ጋር በቅንጅት በመስራት ሀገራዊ የጤና ተልእኮን ለማሳካት በጋራ ከጤና ሣይንስ ኮሌጅ ጋር እየሰራ ይገኛል፡፡ more...