Historical background of DBHSC

የደ/ብርሃን ጤና ሣይንስ ኮሌጅ አመሠራረት እና ታሪካዊ አመጣጡ ከዛሬ 14 ዓመት በፊት በሰሜን ሸዋ ዞን ከደ/ብርሃን ከተማ 17 ኪሎ ሜትር ርቀት አካባቢ የምትገኝ ጐሸባዶ ቀበሌ ገ/ማህበር ውስጥ አንድ ሬድባርና የተባለ ግብረሰናይ ድርጅት የራሱን ተልዕኮ ይዞ ይንቀሳቀስ እንደነበር አንዳንድ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ድርጅቱ የራሱን ኘሮጄክት ከጨረሰ በኋላ ለቢሮ ያዘጋጀውን የአማረና የተዋበ ሕንፃ ለሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ ከነሙሉ ማቴሪያሉ አስረክቦ ነበር ወደመጣበት የተመለሰው ይህ በእንዲህ እንዳለ የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ በክልሉ የሚገኙ ተመላሽ ሠራዊትን ለማጠናከርና አቅማቸውን አጐልብቶ ወደ ሕብረተሰቡ ለማቀላቀል አቅዶ በጤናው ዘርፍ በመከላከያ ሠራዊቱ ውስጥ የመጀመሪያ ሕክምና እርዳታ ሲሰጡ የነበሩ ነገር ግን ምንም ሠርተፊኬት የሌላቸውን መርጦ እነዚህን አካላት ሠርቲፋይድ ለማድረግ አስቦ ለዚህም ስኬት የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ ኃላፊነት ተሰጥቶት ሥራ እንዲጀምር ሲደረግ ነበር፡፡

ያንን ጐሸ ባዶ የሚገኘውን የሬድባርና ጽ/ቤት ለማስተማሪያ አገልግሎት ይውላል ብሎ ያሰበው፡፡ በመሆኑም በ1991 ዓ.ም 5 መምህራንና 22 የአስተዳደር ሠራተኞችን ይዞ 2ዐ ሠልጣኞችን በመቀበል የደ/ብ/መ/ጤ/ባ/ማ/ት/ቤት በሚል ስያሜ የክሊኒካል ነርስ ማሠልጠን ሥራውን አሀዱ ብሎ የጀመረው ይህ በእንዲህ እንዳለ የደ/ብ/መ/ጤ/ባ/ማ/ት/ቤት የተሰጠውን ተግባር ከእለት ወደ እለት በበቂ ሁኔታ እያከናወነ ቢመጣም መሠረታዊ ችግሮች ነበሩበት፡፡

ከእነዚህም ችግሮች ቦታው ለሠራተኞች ከከተማ ራቅ በማለቱ መሠረታዊ የልማት አውታሮች እንደስልክ እና ውሃ፣መብራት ባለመኖራቸው እንደዚሁም ለሠራተኞች መኖሪያና ልዩ ልዩ ለማህበራዊ አገልግሎት የሚሆኑ ነገሮች አልነበሩም ይላሉ የት/ቤቱ የቀድሞ ሠራተኞች የነበረውን ትውስታ ወደ ኋላ እያስታወሱ አንዳንድ ሠራተኞች እንደሚያስታውሱት የተማሪዎች መፀዳጃ ቤት እና ለምግብ ማብሰያ የሚሆን ቤት ሠራተኞቹ በራሣቸው ጉልበት እንደሰሩ ለዚህም ምንም እይታና ማበረታቻ ሣይጠይቁ በፍቅር እንደሰሩት ነው እነ አቶ የማነብርሃን ታደሰ የሚገልፁት ሆኖም ግን እንዲህና እንዲያ እያለ ሥራው በተቀላጠፈ መልኩ እየተሰራ  ቢሆንም ከላይ የጠቀስናቸው መሠረታዊ የልማት  አውታሮች ባለመኖራቸው ምከንያት በተማሪዎችና በሠራተኞች ላይ የሚደርሰው መንገላታት እየጨመረ በመምጣቱ በተለይም በት/ቤቱ ዶርም ለሚኖሩ ተማሪዎች የውሃና የመብራት አገልግሎት ፈተና እየሆነ በመምጣቱ የት/ቤቱ ማኔጅመንት በተደጋጋሚ ለክልሉ ጤና ቢሮ በማቅረባቸውና ት/ቤቱ የሚሰጣቸው ስልጠናዎች ብቃትና ጥራታቸው እየተረጋገጠ በመምጣቱ በሃገራችን ብሎም በክልላችን በየደረጃዉ የሚያስፈልገው በጤናው ዘርፍ የሰለጠነ የሰው ኃይል ፍላጐት በማሟላት ከተጀመሩት የ1ዐ+1፣1ዐ+2፣1ዐ+3 የጤና ባለሙያ ስልጠና መርሃ ግብሮች አንፃር የመካከለኛ ጤና ባለሙያዎች የሚሰለጥኑባቸውን ተቋማት ከማስፋፋት ጐን ለጐን የስልጠናውን ቀጣይነት ማጐልበት ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ እና አላማውንም ከግብ ለማድረስና በሽታን በመከላከል ላይ ያተኮረ የጤና ፖሊስ ተግባራዊ ማድረግና መንግስት በሁሉም መስኮች የቀየሣቸውን የልማት ስትራቴጂዎች በሚገባ ማስፈጸም በማስፈለጉ የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መስተዳድር ም/ቤት በተሻሻለው የክልሉ ሕገ መንግስት አንቀጽ 58 ንዑስ አንቀጽ 7 እና በብሔራዊ ክልላዊ መንግስቱ አስፈጻሚ አካላት እንደገና ማደራጃ እና ስልጣንና ተግባራት መውሰጃ አዋጅ ቁጥር ዐ6/1994ዓ.ም እንደተሻሻለ አንቀጽ 26 ድንጋጌዎች ስር በተሰጠው ሥልጣን መሠረት የደ/ብርሃን ጤና ሣይንስ ኮሌጅ መጠሪያ ስም በደንብ ቁጥር 3ዐ/1997 ዓ.ም ሚያዝያ 3 ቀን 1997 ዓ.ም ተሰይሞ ይኸው እስከአሁን የተጣለበትን ኃላፊነት በብቃትና በጥራት በታማኝነት እየተወጣ የሚገኝ ኮሌጅ ሆኗል፡፡ ወደፊትም የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት እና የብቃት አሀዱን በጨመር ለተሻለ ስኬት አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

Federal Ministry of Health

የፌደራል ጤና ጥበቃ ቢሮ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግና የሕብረተሰቡን የጤና ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ ለማሻሻል ከ21 ጤና ሣይንስ ኮሌጆች ጋር በቅንጅት በመስራት ብቁ የጤና ባለሙያዎችን እንዲያፈሩ፤ ለህብረተሰቡ ችግር ፊቺ የሆኑ ጥናትና ምርምርና የማህበረሰብ የጤና አገልግሎት እንዲሰጡ በተለያየ መልኩ ድጋፍ በማድረግና በቅንጅት በመስራት ሀገራዊ የጤና ተልእኮን ለማሳካት ከጤና ሣይንስ ኮሌጆች ጋር እየሰራ ይገኛል፡፡ more...

Amhara regional health bureau

የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግና የሕብረተሰቡን  የጤና ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ በማሻሻል ረገድ ከጤና ሣይንስ ኮሌጅ ጋር በቅንጅት በመስራት ርህሩህ፣ተገልጋይ አክባሪ እና ሙያዊ ስነ ምግባር የተላበሱ የጤና አገልግሎት ሰጪዎች የማፍራት ስራ፤ ለህብረተሰቡ ችግር ፊቺ የሆኑ ጥናትና ምርምርና የማህበረሰብ የጤና አገልግሎት በመስጠት ከጤና ኮሌጁ ጋር በቅንጅት በመስራት ሀገራዊ የጤና ተልእኮን ለማሳካት በጋራ ከጤና ሣይንስ ኮሌጅ ጋር እየሰራ ይገኛል፡፡ more...