የኮሮና ቫይረስ (COVID 19) ለመከላከል የተሰሩ ስራዎች  

በዓለማችን ብሎም በሀገራችን ከፍተኛ ሰብዓዊ፣ኢኮኖሚያዊ፣ማህበራዊና ስነ-ልቦናዊ ችግር እያስከተለና እየተስፋፋ የመጣውን ኮሮና ቫይረስ ለመከላከል ሀገራዊ ጥሪውን ተቀብሎ ደ/ብርሃን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተለያዩ  ስራዎችን በመስራት ላይ ነው ያሉት የደብረብርሃን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ  ዲን አቶ ማሙዬ መንገሻ፤

  • ቫይረሱን የመከላከል ሥራን በተመለከተ የኮሌጁን ባለሙያዎችን በማቀናጀት የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ በሞንታርቦ ፣ በበራሪ ወረቀቶች አባዝቶ በመስጠት፣ፖስተር እና ባነር በማዘጋጀት ለአካባቢውና ለዞኑን ማህበረሰብ የተሰራ ሲሆን በቀጣይም በተከታታይ የምንሰራው ነው ብለዋል፣
  • 10 (አስር) የሙቀት መለኪያ መሳሪያ (infrared thermometer) በዞኑ ውስጥ ለተመረጡ ጤና ተቋማት ማለትም ለሰ/ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ፣ ለሆስፒታሎች (ደ/ብርሃን፣ ደ/ሲና፣ ሸዋ ሮቢት፣ አጣዬ፣ መ/ሜዳ፣ እናት፣ ደነባ፣ ምንጃር እና ከሚሴ) ተሰራጭቷል፤
  • ለወረርሽኙ መከላከያ የሚሆኑ የእጅ ጓንት (surgical & exam glove)፣ የፊት ጭምብል (face mask)፣ የንፅህና መጠበቂያዎች (የእጅ መታጠቢያ ሳሙና፣ በረኪና) እና ሳኒታይዘር በሰ/ሸዋ ዞን ውስጥ ለሚገኙ ሁሉም ጤና ጣቢያዎች እና ለሁሉም ሆስፒታሎች የተሰራጨ ሲሆን በደ/ብርሃን ከተማ ስር ለተቋቋመ ግብረ ሃይል፣ ለሃበሻ አረጋውያን መርጃ ማዕከል፣ ለሰ/ሸዋ ዞን አካል ጉዳተኞች ማህበር፣ በደ.ብርሃን ሀይለማሪያም ማሞ፣ በመንዝ ቀያ ገብርዔል እና በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ለሚገኙ ተፈናቃዮች አስፈላጊውን የመከላከያ ቁሳቁስ ተሰራጭቷል፡፡

ባጠቃላይ ቫይረሱን ለመከላከል ከ400000 (አራት መቶ ሺህ) ብር በላይ ኮሌጁ ድጋፍ ያደረገ ሲሆን በቀጣይም እንደአሰፈላጊነቱ የተለያዩ ድጋፎችን በዞኑ ከተቋቋመው ግብረ ሃይል ጋር በመነጋገር የሚያደርግ መሆኑን የኮሌጁ ዲን አቶ ማሙዬ መንገሻ ተናግረዋል፡፡ ...

 

Federal Ministry of Health

የፌደራል ጤና ጥበቃ ቢሮ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግና የሕብረተሰቡን የጤና ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ ለማሻሻል ከ21 ጤና ሣይንስ ኮሌጆች ጋር በቅንጅት በመስራት ብቁ የጤና ባለሙያዎችን እንዲያፈሩ፤ ለህብረተሰቡ ችግር ፊቺ የሆኑ ጥናትና ምርምርና የማህበረሰብ የጤና አገልግሎት እንዲሰጡ በተለያየ መልኩ ድጋፍ በማድረግና በቅንጅት በመስራት ሀገራዊ የጤና ተልእኮን ለማሳካት ከጤና ሣይንስ ኮሌጆች ጋር እየሰራ ይገኛል፡፡ more...

Amhara regional health bureau

የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግና የሕብረተሰቡን  የጤና ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ በማሻሻል ረገድ ከጤና ሣይንስ ኮሌጅ ጋር በቅንጅት በመስራት ርህሩህ፣ተገልጋይ አክባሪ እና ሙያዊ ስነ ምግባር የተላበሱ የጤና አገልግሎት ሰጪዎች የማፍራት ስራ፤ ለህብረተሰቡ ችግር ፊቺ የሆኑ ጥናትና ምርምርና የማህበረሰብ የጤና አገልግሎት በመስጠት ከጤና ኮሌጁ ጋር በቅንጅት በመስራት ሀገራዊ የጤና ተልእኮን ለማሳካት በጋራ ከጤና ሣይንስ ኮሌጅ ጋር እየሰራ ይገኛል፡፡ more...