የኮሌጁ ራዕይ /Vision/

የመማር ማስተማር ደረጃውን ከመካከለኛ ጤና ባለሙያዎች ሥልጠና ወደ ከፍተኛ ደረጃ አድጐ ከፍተኛ የጤና ባለሙያዎች የሚፈሩበት እንዲሁም ጤና ነክ ጥናትና ምርምር የሚካሄድበት ማዕከል ሆኖ ማየት፡፡

የኮሌጁ ተልዕኮ /Mission/

በክልሉ ውስጥ በሽታዎችንና  አደጋዎችን  ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል  ስልትን  በመንደፍ  የህብረተሰቡን የጤና ችግር መቅረፍ የሚችሉ፣የጋራ አሰራርን የሚከተሉ፣ብቃት ያላቸው በሙያ ስነምግባር የታነፁ የመካከለኛ ደረጃ የጤና ባለሙያዎችን ማፍራት፡፡

እሴቶች /Values/

  • ከሁለም በፊት ሠልጣኝ ተማሪዎች ቅድሚያ መስጠት
  • ከአድሎዎና ሙስና ነፃ የሆነ ስልጠና መስጠት
  • የህክምና ስነ-ምግባርን በተላበሰ መልኩ ሠልጣኞችን መቅረፅ
  • ገንዘብን ፣ ንብረትንና ጊዜን በአግባቡና በቁጠባ መጠቀም
  • ስራን ፈጥሮ የመስራት ችሎታን ማሳደግ ተነሳሽነት ከፍ ማድረግ
  • በጤናው ዘርፍ በአካባቢ ሊገኙ እና ሊሰራባቸው የሚችሉ ተስማሚ ቴክኖሎጂ መጠቀም
  • ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ያለበት አሰራር መከተል
  • ህብረተሰቡን አግባብነት ያለው የጤና አገልግሎት የማግኘት መብቱን ማረጋገጥ

Federal Ministry of Health

የፌደራል ጤና ጥበቃ ቢሮ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግና የሕብረተሰቡን የጤና ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ ለማሻሻል ከ21 ጤና ሣይንስ ኮሌጆች ጋር በቅንጅት በመስራት ብቁ የጤና ባለሙያዎችን እንዲያፈሩ፤ ለህብረተሰቡ ችግር ፊቺ የሆኑ ጥናትና ምርምርና የማህበረሰብ የጤና አገልግሎት እንዲሰጡ በተለያየ መልኩ ድጋፍ በማድረግና በቅንጅት በመስራት ሀገራዊ የጤና ተልእኮን ለማሳካት ከጤና ሣይንስ ኮሌጆች ጋር እየሰራ ይገኛል፡፡ more...

Amhara regional health bureau

የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግና የሕብረተሰቡን  የጤና ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ በማሻሻል ረገድ ከጤና ሣይንስ ኮሌጅ ጋር በቅንጅት በመስራት ርህሩህ፣ተገልጋይ አክባሪ እና ሙያዊ ስነ ምግባር የተላበሱ የጤና አገልግሎት ሰጪዎች የማፍራት ስራ፤ ለህብረተሰቡ ችግር ፊቺ የሆኑ ጥናትና ምርምርና የማህበረሰብ የጤና አገልግሎት በመስጠት ከጤና ኮሌጁ ጋር በቅንጅት በመስራት ሀገራዊ የጤና ተልእኮን ለማሳካት በጋራ ከጤና ሣይንስ ኮሌጅ ጋር እየሰራ ይገኛል፡፡ more...