የደ/ብርሃን ጤና ሣይንስ ኮሌጅ በተለያየ ሙያ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ፡፡

የደ/ብርሃን ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ግንቦት 15/2013 ዓ.ም. የተማሪዎች የምረቃ በዓል አከናውኗል፡፡የኮሌጁ መመህራንና ሠራተኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች እና የተመራቂ ቤተሰቦች በተገኙበት ነው የምርቃት ስነስርአቱ የተካሄደው፡፡  የኮሌጁ ዲን አቶ ማሙዬ መንገሻ ባደረጉት ንግግር ትምህርት የአንድ ሀገር ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ እድገት ለማምጣት የሚረዳ ቁልፍ መሣሪያ በመሆኑ ኮሌጃችንም ይህንን በመረዳት ጥራት ያለው፣ደረጃውን የጠበቀና ውጤት ሊያመጣ የሚችል ሥልጠና በመስጠት ብቃት ያላቸው ህብረተሰቡን በቅንነትና በታማኝነት የሚያገለግሉ የጤና ባለሙያዎችን ለማፋራት አላማዬ ብሎ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡

የደ/ብርሃን ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ቀደም ሲል በመለስተኛ ጤና ባለሙያዎች ማሠልጠኛ ት/ቤትነት በ1991 ዓ.ም የተመሠረተ ሲሆን በ1997 ዓ.ም ከክልሉ መንግስትና ከጤና ጥበቃ ቢሮ በተሰጠው ልዩ ትኩረት ወደ ጤና ኮሌጅነት ያደገ ኮሌጅ ነው፡፡

ኮሌጁ ከ1991 ዓ.ም እስከ 2013 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 415 መለስተኛ ክሊኒካል ነርሶች ፣ 1421 ክሊኒካል ነርሶች፣629 ፋርማሲ ቴክኒሽያኖች፣ 387 ጤና መረጃ ቴክኒሽያን፣555 ሚድዋይፍሪይ፣ደረጃ 4 እና ደረጃ3 ጤና ኤክስቴንሽን 1869፣48 ድንገተኛ ህክምና ቴክኒሻያን 44 የላብራቶሬ ባለሙያዎችን በድማሩ 5461 የጤና ባለሙያዎችን በዲኘሎማ ደረጃ በማሠልጠንና በማስመረቅ የክልላችንን የጤና ባሙያ ችግር በመቅረፍ የበኩሉን እየተወጣ ይገኛል፡፡
ኮሌጁ በ2013 ዓ.ም በተለያየ ጊዜ 47 የፋርማሲ፣47 የነርስ፣47 የሚድዋይፍሪይ  እና 39 የጤና መረጃ ባለሙያዎችን ያስመረቀ ሲሆን በዛሬው ዕለት ለ3 ተከታታይ ዓመታት ያሰለጠናቸውን 242 የደረጃ 4 ጤና ኤክስቴንሽን እና 94 የኣካባቢጤና አጠባበቅ ወይም የኢንቫይሮሜንታል ባለሙዎችን በድምሩ 336 የጤና ባለሙያዎችን የሚያስመርቅ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 81 ፐርሰንት የሚሆኑት ሴቶች ናቸው፡፡

ኮሌጁ በስምንት የተለያዩ የሙያ ዓይነቶች ማለትም በክሊኒካል ነርስ ፣ በላብራቶሪና አንስቴዥያ፣ በአካባቢ ጤና አጠባበቅ ትምህርት፣በፋርማሲ ቴክኒሽያን፣ በሚድዋይፍሪይ፣ በጤና መረጃ ቴክኒሽያን እና በጤና ኤክስቴንሽን ትምህርት እየሰጠ ይገኛል፡፡ ይህን ትምህርት በመስጠት ላይ ያሉ 3ዐ የሁለተኛ ዲግሪ  31 የመጀመሪያ ዲግሪ እና 7 ዲኘሎማ ያላቸው መምህራን ሲኖሩ በድምሩ መማር ማስተማሩ በ68 መምህራን እየተሰጠ ሲሆን የድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች 41 ሲሆኑ በድምሩ 1ዐ9 የሰው ኃይል በመያዝ የመማር ማስተማሩን እያከናወነ ይገኛል፡፡
ኮሌጃችን የመማር ማስተማሩን ጥራት ለመጠበቅ፡ ተማሪዎቹን በስነምግባር የታነፁ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የትምህርት ልማት ማዕከል/EDC/ በመመስረት በመምህራን ልማት፣ካሪኩለም ክለሳ፣በትምህርት ጥራት ማረጋጋጥና በምርምር ቡድን በመክፈል የትምህርት ጥራት ያለበትን በማወቅ፣ክትትል በማድረግና ደረጃውን የጠበቀ መማር ማስተማር እንዲኖር ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ አጠቃላይ የብቃት ምዘና ውጤት 85% በላይ ማድረስ የተቻለበት ሁኔታ ላይ ተደርሷል፡፡ በተጨማሪም የሀገራችን የስራ ላይ ስልጠና ደረጃውን የጠበቀና ተቋማዊ ለማድረግና የተነደፈውን ሀገራዊ የተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ ንድፈ ሃሳብ  በመቀበልና ለመተግበር ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እና  የስራ ላይ ስልጠና በመስጠት የጤና አገልግሎት ጥራቱን በማስጠበቅ ላይ ይገኛል፡፡

ኮሌጃችን ይህን የመማር ማስተማር እንቅስቃሴ ከዚህ በላይ በትምህርት አይነትም ሆነ ከደረጃ አራት ወደ ድግሪ የማሣደግ  እቅድ እና ፍላጐት ቢኖረውም የመማሪያ ክፍሎች፣የሠርቶ ማሣያ ክፍሎችና የመመህራን ቢሮዎች ችግር ኮሌጁን ለማስፋፋት የቦታ እጥረት እና በክልሉ መንግስት የሚፈቱ የአወጅ እና የመመሪያ ማሻሻያወች ማነቆ በመሆናቸው የሚመለከታቸው ሁሉ በዚህ አጋጣሚ ፈጣን ምላሽ እንዲሰጡን አቶ ማሙዬ መንገሻ ባደረጉት ንግግር አሳስበዋል፡፡
በምረቃ ስርዓቱ ላይ ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ተማሪዎች ሽልማት የተሰጠ ሲሆን በመጨረሻም ውድ ተመሪቂዎች በኮሌጁ ቆይታችው ባገኙትት እውቀት ላይ የራሣችውን ጥረት በማከል ከሁሉም በላይ ክቡር የሆነውን የሰው ልጅ ለመንከባከብና የጤና ችግሮችን ለመቅረፍ ደከመኝ ሰለቸኝ ሣይሉ ሙያችው በሚፈቅድላችው ሁሉ በቅንነት፣በታማኝነት እንዲያገለግሉ የቃለ-መሃላ ስነ

ስርዓት የተካሄደ ከመሆኑ በተጨማሪ የእለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት የሰ/ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፀዳለ ሰሙንጉስ ይህንኑ ለተመራቂዎች በአደራ ጭምር አሳሰበው መጪው ዘመን ጥሩ የሥራ ጊዜ እንዲሆንላችሁ ተመኝተዋል፡፡በአጠቃላይ የመማር ማስተማር ሂደቱን ከግቡ እንዲደርስ ድጋፍ ላደረጉልን መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ኮሌጁ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርቧል፡

Federal Ministry of Health

የፌደራል ጤና ጥበቃ ቢሮ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግና የሕብረተሰቡን የጤና ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ ለማሻሻል ከ21 ጤና ሣይንስ ኮሌጆች ጋር በቅንጅት በመስራት ብቁ የጤና ባለሙያዎችን እንዲያፈሩ፤ ለህብረተሰቡ ችግር ፊቺ የሆኑ ጥናትና ምርምርና የማህበረሰብ የጤና አገልግሎት እንዲሰጡ በተለያየ መልኩ ድጋፍ በማድረግና በቅንጅት በመስራት ሀገራዊ የጤና ተልእኮን ለማሳካት ከጤና ሣይንስ ኮሌጆች ጋር እየሰራ ይገኛል፡፡ more...

Amhara regional health bureau

የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግና የሕብረተሰቡን  የጤና ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ በማሻሻል ረገድ ከጤና ሣይንስ ኮሌጅ ጋር በቅንጅት በመስራት ርህሩህ፣ተገልጋይ አክባሪ እና ሙያዊ ስነ ምግባር የተላበሱ የጤና አገልግሎት ሰጪዎች የማፍራት ስራ፤ ለህብረተሰቡ ችግር ፊቺ የሆኑ ጥናትና ምርምርና የማህበረሰብ የጤና አገልግሎት በመስጠት ከጤና ኮሌጁ ጋር በቅንጅት በመስራት ሀገራዊ የጤና ተልእኮን ለማሳካት በጋራ ከጤና ሣይንስ ኮሌጅ ጋር እየሰራ ይገኛል፡፡ more...