ኮሌጁ ማህበረሰብ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ

የክልሉ የሰለጠነ የሰው ኃይል ፍላጎት በማሟላት በጤናው ዙሪያ አኩሪ ተግባር እየፈፀመ ያለው ኮሌጃችን አሁንም የት/ት ስትራቴጂውን በመቀየስ ይህንኑ ተግባሩን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ለዚህም የትምህርት ጥራትን አስጠብቆ በቂ ልምድና እውቀትን ማዳበር አስፈላጊ መሆኑ ይታመናል፡፡ ለዚህ ነው እንግዲህ የደ/ብርሃን ጤና ሳይንስ ኮሌጅም ለመምህራኑ እና ለሠራተኞቹ የተለያዩ የአቅም መገንቢያ ስልጠናዎችን ከተለያዩ አካላት ጋር በመገናኘት አጫጭር ስልጠናዎችን በበጀት አመቱ የሰጠው ለዚህም ተግባር

  • በፊስቱላ መካ/ተሃድሶ ህክምና
  • በምዘና ስነ ዘዴ 
  • በግዥና ንብረት አስተዳደር ዙሪያ
  • በ Simulation work training ች
  • በ Effective training skill 
  • በሚድዋይፈሪ ፕሮግራም ዙሪያ 
  • በworkshop & Advocacy workshop 
  • በሄልዝ ኤክስቴንሽን 
  • በሄልዝ ኤክስቴንሽን የሙያ ማሻሻያ እና Research methodology Ethics
  • በሰው ሃይል ስምሪትና በዲሲፕሊን መመሪያ 
  • በኤች አይቪ ኤድስ ዙሪያ 
  • በልማት ሠራዊት መመሪያ በዜጎች ቻርተር በምርጥ ተሞክሮ
  • በBSC እና በመንግስት ሠራተኞች የአፈፃፀም ምዘና እና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ 
  • Gender & Assertiveness

በአጠቃላይ በ15 አይነት ስልጠናዎች 50 ሰዎችን በመስክ የሙያ ማሻሻያ ስልጠናዎችን ሲሰጥ ከደ/ብርሃን ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ለ18 መምህራን /የHDP/ Higher Diploma ት/ት አሰጥቷል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከ18 በላይ ለሆኑ ለአስተዳደር ሠራተኞችና መምህራንም የኮምፒዩተር Skill ት/ት የሰጠ በመሆኑ ኮሌጁ የሚሊኒየሙን ግብ ለማሳካት እና ራዕዩን እውን ለማድረግ ኮሌጁ ጠንክሮ እየሠራ ነው፡፡

Federal Ministry of Health

የፌደራል ጤና ጥበቃ ቢሮ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግና የሕብረተሰቡን የጤና ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ ለማሻሻል ከ21 ጤና ሣይንስ ኮሌጆች ጋር በቅንጅት በመስራት ብቁ የጤና ባለሙያዎችን እንዲያፈሩ፤ ለህብረተሰቡ ችግር ፊቺ የሆኑ ጥናትና ምርምርና የማህበረሰብ የጤና አገልግሎት እንዲሰጡ በተለያየ መልኩ ድጋፍ በማድረግና በቅንጅት በመስራት ሀገራዊ የጤና ተልእኮን ለማሳካት ከጤና ሣይንስ ኮሌጆች ጋር እየሰራ ይገኛል፡፡ more...

Amhara regional health bureau

የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግና የሕብረተሰቡን  የጤና ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ በማሻሻል ረገድ ከጤና ሣይንስ ኮሌጅ ጋር በቅንጅት በመስራት ርህሩህ፣ተገልጋይ አክባሪ እና ሙያዊ ስነ ምግባር የተላበሱ የጤና አገልግሎት ሰጪዎች የማፍራት ስራ፤ ለህብረተሰቡ ችግር ፊቺ የሆኑ ጥናትና ምርምርና የማህበረሰብ የጤና አገልግሎት በመስጠት ከጤና ኮሌጁ ጋር በቅንጅት በመስራት ሀገራዊ የጤና ተልእኮን ለማሳካት በጋራ ከጤና ሣይንስ ኮሌጅ ጋር እየሰራ ይገኛል፡፡ more...