የ ል ም ድ ል ው ው ጥ
እንደሚታወቀው ሃገራችንን የነደፈችውን የ5 አመት የእድገትና የትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማሳካት ሁሉም ሴክተሮች ደፋ ቀና ማለት ከጀመሩ ውለው አድረዋል፡፡
ከነዚህም ሴክተሮች ደግሞ የደ/ብርሃን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ አንዱ እና ዋናው የእውቀት ምንጭ መሆኑ ግልጽ ነው፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ ኮሌጃችን በተለያዩ ዲፓርትመንቶች እያሰለጠነ የሚያስመርቃቸው ተማሪዎች በበቂ መምህራን እና ሠራተኞች በተደገፈ እውቀትና ልምድ በመሆኑ ይህንን ሥራውን አጠናክሮ ለማስቀጠል ከአጋር ኮሌጆች ጋር የልምድ ልውውጥ ማድረግና መልካም የሚባሉ ተሞክሮዎችን ቀምሮ በማምጣት ወደ ራሱ ቀይሮ የት/ት ጥራቱን አስጠብቆ ሃገሪቱና ክልሉ የሚፈልጋቸውን የጤና ባለሙያዎች ብቁ አድርጎ ለማውጣት ይጠቅመው ዘንድ በ3 ክልሎች የሚገኙ አጋር
የጤና ሳይንስ ኮሌጆችን መርጦ 13 አባላትን ያካተተ መምህራንን እና የአስተዳደር ሠራተኞችን ነበር ወደ ፍቼ ሰላሌ፣አዲስ አበባ ዳግማዊ ምኒሊክ እንዲሁም ሻሸመኔ እና አዋሳ ጤና ሳይንስ ኮሌጆች የላከው ታዲያ ይህ ቡድን 5 ቀናትን የፈጀ ጉዞ አድርጎ መልካም የሚላቸውን ተግባራት በመውሰድ እንዲሁም በደ/ብርሃን ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የተሻሉ ተሞክሮዎችን በማካፈል ነበር የተመለሰው ከዚህም ጉብኝት የተገኙ መልካም ተሞክሮዎች በበጀት አጠቃቀም በ Internal COC በመማር ማስተማሩ እና በተለያዩ አደረጃጀቶች ያገኛቸውን ከራሱ አሰራር ጋር በማጣመር ይኸው አንቱ የሚያሰኘውን ተግባር እየፈፀመ ያለ ኮሌጅ ነው፡፡
ሆኖም ግን ኮሌጁ ካለበት የኢንፍራስትራክቸር አቀማመጥ ችግር የተነሳ ያቀደውን ብቻ እያከናወነ ሌሎች አዳዲስ ፈጠራዎችን ለመስራት ያልቻለ መሆኑን ለማንም ግልፅ ነው፡፡ በመሆኑም ወደፊት የራሱ የሆነ ህንፃ ሲኖረው የት/ት አሰጣጡን ወደ ዲግሪ ከፍ ለማድረግና የተለያዩ ዲፓርትመንቶች በመክፈት እና ክልሉ የሚፈልጋቸውን የጤና ባለሙያዎች እጥረት ለመቅረፍ አቅዶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡