የኮቪድ-19 ምልክቶች
በአብዛኛው ጊዜ የሚታዩ የኮቪድ-19 ምልክቶች፡
? ትኩሳት
? ድካም
? ደረቅ ሳል
አንዳንድ በሽተኞች ህመም ሊሰማቸው ይችላል፤ የአፍንጫ መደፈን ወይም ፈሳሽ መብዛት የጉሮሮ ህመም እና ተቅማጥ ሊኖራቸው ይችላል:: በአብዛኛው እነዚህ ምልክቶች መለስተኛ እና ቀስ በቀስ መታየት የሚጀምሩ ናቸው፤ አንዳንድ ሰዎች በበሽታው ቢያዙም እነዚህ ምልክቶችም ሆኑ የህመም ስሜት ላይሰማቸው ይችላል:: ብዙ ሰዎች (80% ያህል) የተለየ ህክምና ሳያስፈልጋቸው ከበሽታው ሊያገግሙ ይችላሉ በኮቪድ-19 ከሚያዙ ሰዎች አንድ ስድስተኛ የሚሆኑት በጠና ታመው የመተንፈስ እክል ያጋጥማቸዋል:: በእድሜ የገፉ ሰዎች እና እንደ ደም ግፊት፥ የልብ ወይም የስዃር በሽታ ተጠቂ የሆኑ ሰዎች በጠና ሊታመሙ ይችላሉ::
Source: Ministry of Health, Ethiopia