የኮሮና ቫይረስ እውነታዎች

በኮሮና ቫይረስ ዙርያ ያሉ የተሳሳቱ ግንዛቤዎች!

1. ኮሮና ቫይረስ የሚያጠቃው አረጋዊያንን ብቻ ነው

ስሕተት

የኮሮና ቫይረስ ዘርን፣ ቀለምን፣ ዕድሜን ሳይለይ ማንንም ይይዛል። ነገር ግን አረጋዊያንን ይበልጥ ለከፋ ጉዳት ያደርሳል የሚል አጠቃላይ ግምት ብቻ ነው ያለው።

በተጨማሪም የሳምባ፣ የጉበት፣ የኩላሊት፣ የልብ ሕመሞች፣ ካንሰር፣ ኤድስ፣ ስኳር በሽታ ወዘተ ያለባቸውን ሕሙማን በከፍተኛ ሁኔታ ይጎዳል። ወጣቶችም አናመልጥም፣ እንጠንቀቅ።


 2. የቤት እንስሳት ኮሮናቫይረስን ያሰራጫሉ

ስሕተት

እስካሁን ባለው ሁኔታ ከውሻ፣ ድመት ወዘተ ወደ ሰው ተላልፎ የተከሰተ የዚህ በሽታ ሪፖርት የለም። ሆኖም ግን ከነሱ ጋርም ሆነ ተቀምጠን ከተነሣንም፣ የእጃችንን ሁሉንም ክፍል በሳሙና ለ20 ሰኮንድ መታጠብ ለጥንቃቄ ያግዛል።


 3. የተለያዩ ባሕላዊ መድኃኒቶች፣ ቫይታሚኖች ከቫይረሱ ያድናሉ

ስሕተት

እስካሁን በሳይንስ የተረጋገጠ መድኃኒትም፣ ክትባትም የለም። በቅርብ የምናይ ይሆናል። ቫይታሚንና የተለያዩ የሰውነት የመከላከል አቅምን የሚጨምሩ ምግቦችን መውሰድ ጥሩ ነው። ግን በሽታው እንዳይዘን አያደርጉንም።


 4. መድኃኒቶች (antibiotics) ከኮሮና ቫይረስ በሽታ ያድናሉ

ስሕተት

በኮሮና ቫይረስ በሽታ የታመሙ ሰዎች አንታይባዮቲክስ የሚወስዱት ተጨማሪ ኢንፌክሺን ሲኖራቸው ነው። አንታይባዮቲክስ ከኮረናቫይረስ እንደሚያድን ሳይንስ አላረጋገጠም። 


 5. Surgical Mask መጠቀም ከኮሮናቫይረስ በበቂ ሁኔታ ይከላከላል

ስሕተት

- የፊትና የአፍ ማስክ መጠቀም ያለበት በሽታው ያለበትና የጤና ባለሙያ ነው። ሌላ ሰው (N95 የሚባለውን ማስክ ጨምሮ) ባይጠቀም ይመረጣል። ምክንያት:

- disposable surgical masks በአየር የሚመጡ ጎጂ ኢንፌክሺኖችን ለመከላከል ፊትን ሙሉ በሙሉ አይሸፍኑም፣ ሰለዚህ በቀላሉ እንጠቃለን።

- በተደጋጋሚ እያወለቅን፣ እየነካካነው ለረጅም ጊዜ በተለይ ጸሐያማ ወይም ሙቀት ያለበት ቦታ ከተጠቀምነው ይበልጥ ለኢንፌክሽኑ ያጋልጡናል እንጂ አያድኑንም። 


 

ዋናው!

እጃችሁን ታጠቡ፣ ማኅበራዊ ፈቀቅታን ተግባራዊ አድርጉ፣ ሰው የተሰበሰበት ቦታ አትሂዱ፣ እጅ መታጠቢያ ቦታ ለመታጠብ አትሰለፉ፣ አትጋፉ፣ የበሽታው ምልክት ያለበት ሰው ቶሎ የሕክምና አገልግሎትን ያግኝ።

Federal Ministry of Health

የፌደራል ጤና ጥበቃ ቢሮ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግና የሕብረተሰቡን የጤና ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ ለማሻሻል ከ21 ጤና ሣይንስ ኮሌጆች ጋር በቅንጅት በመስራት ብቁ የጤና ባለሙያዎችን እንዲያፈሩ፤ ለህብረተሰቡ ችግር ፊቺ የሆኑ ጥናትና ምርምርና የማህበረሰብ የጤና አገልግሎት እንዲሰጡ በተለያየ መልኩ ድጋፍ በማድረግና በቅንጅት በመስራት ሀገራዊ የጤና ተልእኮን ለማሳካት ከጤና ሣይንስ ኮሌጆች ጋር እየሰራ ይገኛል፡፡ more...

Amhara regional health bureau

የአማራ ክልል ጤና ጥበቃ ቢሮ የጤና አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግና የሕብረተሰቡን  የጤና ሁኔታ በከፍተኛ ደረጃ በማሻሻል ረገድ ከጤና ሣይንስ ኮሌጅ ጋር በቅንጅት በመስራት ርህሩህ፣ተገልጋይ አክባሪ እና ሙያዊ ስነ ምግባር የተላበሱ የጤና አገልግሎት ሰጪዎች የማፍራት ስራ፤ ለህብረተሰቡ ችግር ፊቺ የሆኑ ጥናትና ምርምርና የማህበረሰብ የጤና አገልግሎት በመስጠት ከጤና ኮሌጁ ጋር በቅንጅት በመስራት ሀገራዊ የጤና ተልእኮን ለማሳካት በጋራ ከጤና ሣይንስ ኮሌጅ ጋር እየሰራ ይገኛል፡፡ more...