የኮሌጁ ራዕይ /Vision/
የመማር ማስተማር ደረጃውን ከመካከለኛ ጤና ባለሙያዎች ሥልጠና ወደ ከፍተኛ ደረጃ አድጐ ከፍተኛ የጤና ባለሙያዎች የሚፈሩበት እንዲሁም ጤና ነክ ጥናትና ምርምር የሚካሄድበት ማዕከል ሆኖ ማየት፡፡
የኮሌጁ ተልዕኮ /Mission/
በክልሉ ውስጥ በሽታዎችንና አደጋዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያስችል ስልትን በመንደፍ የህብረተሰቡን የጤና ችግር መቅረፍ የሚችሉ፣የጋራ አሰራርን የሚከተሉ፣ብቃት ያላቸው በሙያ ስነምግባር የታነፁ የመካከለኛ ደረጃ የጤና ባለሙያዎችን ማፍራት፡፡
እሴቶች /Values/
- ከሁለም በፊት ሠልጣኝ ተማሪዎች ቅድሚያ መስጠት
- ከአድሎዎና ሙስና ነፃ የሆነ ስልጠና መስጠት
- የህክምና ስነ-ምግባርን በተላበሰ መልኩ ሠልጣኞችን መቅረፅ
- ገንዘብን ፣ ንብረትንና ጊዜን በአግባቡና በቁጠባ መጠቀም
- ስራን ፈጥሮ የመስራት ችሎታን ማሳደግ ተነሳሽነት ከፍ ማድረግ
- በጤናው ዘርፍ በአካባቢ ሊገኙ እና ሊሰራባቸው የሚችሉ ተስማሚ ቴክኖሎጂ መጠቀም
- ግልፀኝነትና ተጠያቂነት ያለበት አሰራር መከተል
- ህብረተሰቡን አግባብነት ያለው የጤና አገልግሎት የማግኘት መብቱን ማረጋገጥ