የደ/ብርሃን ጤና ሣይንስ ኮሌጅ በተለያየ ሙያ ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች አስመረቀ፡፡
የደ/ብርሃን ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ግንቦት 15/2013 ዓ.ም. የተማሪዎች የምረቃ በዓል አከናውኗል፡፡የኮሌጁ መመህራንና ሠራተኞች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላችሁ እንግዶች እና የተመራቂ ቤተሰቦች በተገኙበት ነው የምርቃት ስነስርአቱ የተካሄደው፡፡ የኮሌጁ ዲን አቶ ማሙዬ መንገሻ ባደረጉት ንግግር ትምህርት የአንድ ሀገር ማህበራዊ፣ኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊ እድገት ለማምጣት የሚረዳ ቁልፍ መሣሪያ በመሆኑ ኮሌጃችንም ይህንን በመረዳት ጥራት ያለው፣ደረጃውን የጠበቀና ውጤት ሊያመጣ የሚችል ሥልጠና በመስጠት ብቃት ያላቸው ህብረተሰቡን በቅንነትና በታማኝነት የሚያገለግሉ የጤና ባለሙያዎችን ለማፋራት አላማዬ ብሎ እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ጠቅሰዋል፡፡
የደ/ብርሃን ጤና ሣይንስ ኮሌጅ ቀደም ሲል በመለስተኛ ጤና ባለሙያዎች ማሠልጠኛ ት/ቤትነት በ1991 ዓ.ም የተመሠረተ ሲሆን በ1997 ዓ.ም ከክልሉ መንግስትና ከጤና ጥበቃ ቢሮ በተሰጠው ልዩ ትኩረት ወደ ጤና ኮሌጅነት ያደገ ኮሌጅ ነው፡፡
ኮሌጁ ከ1991 ዓ.ም እስከ 2013 ዓ.ም መጨረሻ ድረስ በተለያዩ የሙያ መስኮች ያሰለጠናቸውን 415 መለስተኛ ክሊኒካል ነርሶች ፣ 1421 ክሊኒካል ነርሶች፣629 ፋርማሲ ቴክኒሽያኖች፣ 387 ጤና መረጃ ቴክኒሽያን፣555 ሚድዋይፍሪይ፣ደረጃ 4 እና ደረጃ3 ጤና ኤክስቴንሽን 1869፣48 ድንገተኛ ህክምና ቴክኒሻያን 44 የላብራቶሬ ባለሙያዎችን በድማሩ 5461 የጤና ባለሙያዎችን በዲኘሎማ ደረጃ በማሠልጠንና በማስመረቅ የክልላችንን የጤና ባሙያ ችግር በመቅረፍ የበኩሉን እየተወጣ ይገኛል፡፡
ኮሌጁ በ2013 ዓ.ም በተለያየ ጊዜ 47 የፋርማሲ፣47 የነርስ፣47 የሚድዋይፍሪይ እና 39 የጤና መረጃ ባለሙያዎችን ያስመረቀ ሲሆን በዛሬው ዕለት ለ3 ተከታታይ ዓመታት ያሰለጠናቸውን 242 የደረጃ 4 ጤና ኤክስቴንሽን እና 94 የኣካባቢጤና አጠባበቅ ወይም የኢንቫይሮሜንታል ባለሙዎችን በድምሩ 336 የጤና ባለሙያዎችን የሚያስመርቅ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 81 ፐርሰንት የሚሆኑት ሴቶች ናቸው፡፡
ኮሌጁ በስምንት የተለያዩ የሙያ ዓይነቶች ማለትም በክሊኒካል ነርስ ፣ በላብራቶሪና አንስቴዥያ፣ በአካባቢ ጤና አጠባበቅ ትምህርት፣በፋርማሲ ቴክኒሽያን፣ በሚድዋይፍሪይ፣ በጤና መረጃ ቴክኒሽያን እና በጤና ኤክስቴንሽን ትምህርት እየሰጠ ይገኛል፡፡ ይህን ትምህርት በመስጠት ላይ ያሉ 3ዐ የሁለተኛ ዲግሪ 31 የመጀመሪያ ዲግሪ እና 7 ዲኘሎማ ያላቸው መምህራን ሲኖሩ በድምሩ መማር ማስተማሩ በ68 መምህራን እየተሰጠ ሲሆን የድጋፍ ሰጪ ሠራተኞች 41 ሲሆኑ በድምሩ 1ዐ9 የሰው ኃይል በመያዝ የመማር ማስተማሩን እያከናወነ ይገኛል፡፡
ኮሌጃችን የመማር ማስተማሩን ጥራት ለመጠበቅ፡ ተማሪዎቹን በስነምግባር የታነፁ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራትን እያከናወነ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ የትምህርት ልማት ማዕከል/EDC/ በመመስረት በመምህራን ልማት፣ካሪኩለም ክለሳ፣በትምህርት ጥራት ማረጋጋጥና በምርምር ቡድን በመክፈል የትምህርት ጥራት ያለበትን በማወቅ፣ክትትል በማድረግና ደረጃውን የጠበቀ መማር ማስተማር እንዲኖር ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ አጠቃላይ የብቃት ምዘና ውጤት 85% በላይ ማድረስ የተቻለበት ሁኔታ ላይ ተደርሷል፡፡ በተጨማሪም የሀገራችን የስራ ላይ ስልጠና ደረጃውን የጠበቀና ተቋማዊ ለማድረግና የተነደፈውን ሀገራዊ የተከታታይ ሙያ ማጎልበቻ ንድፈ ሃሳብ በመቀበልና ለመተግበር ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እና የስራ ላይ ስልጠና በመስጠት የጤና አገልግሎት ጥራቱን በማስጠበቅ ላይ ይገኛል፡፡
ስርዓት የተካሄደ ከመሆኑ በተጨማሪ የእለቱ የክብር እንግዳ የሆኑት የሰ/ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ ም/ኃላፊ ወ/ሮ ፀዳለ ሰሙንጉስ ይህንኑ ለተመራቂዎች በአደራ ጭምር አሳሰበው መጪው ዘመን ጥሩ የሥራ ጊዜ እንዲሆንላችሁ ተመኝተዋል፡፡በአጠቃላይ የመማር ማስተማር ሂደቱን ከግቡ እንዲደርስ ድጋፍ ላደረጉልን መንግስታዊና መንግስታዊ ላልሆኑ ድርጅቶች ኮሌጁ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርቧል፡