ኮሌጁ ማህበረሰብ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ
የክልሉ የሰለጠነ የሰው ኃይል ፍላጎት በማሟላት በጤናው ዙሪያ አኩሪ ተግባር እየፈፀመ ያለው ኮሌጃችን አሁንም የት/ት ስትራቴጂውን በመቀየስ ይህንኑ ተግባሩን አጠናክሮ ቀጥሏል፡፡ ለዚህም የትምህርት ጥራትን አስጠብቆ በቂ ልምድና እውቀትን ማዳበር አስፈላጊ መሆኑ ይታመናል፡፡ ለዚህ ነው እንግዲህ የደ/ብርሃን ጤና ሳይንስ ኮሌጅም ለመምህራኑ እና ለሠራተኞቹ የተለያዩ የአቅም መገንቢያ ስልጠናዎችን ከተለያዩ አካላት ጋር በመገናኘት አጫጭር ስልጠናዎችን በበጀት አመቱ የሰጠው ለዚህም ተግባር
- በፊስቱላ መካ/ተሃድሶ ህክምና
- በምዘና ስነ ዘዴ
- በግዥና ንብረት አስተዳደር ዙሪያ
- በ Simulation work training ች
- በ Effective training skill
- በሚድዋይፈሪ ፕሮግራም ዙሪያ
- በworkshop & Advocacy workshop
- በሄልዝ ኤክስቴንሽን
- በሄልዝ ኤክስቴንሽን የሙያ ማሻሻያ እና Research methodology Ethics
- በሰው ሃይል ስምሪትና በዲሲፕሊን መመሪያ
- በኤች አይቪ ኤድስ ዙሪያ
- በልማት ሠራዊት መመሪያ በዜጎች ቻርተር በምርጥ ተሞክሮ
- በBSC እና በመንግስት ሠራተኞች የአፈፃፀም ምዘና እና አገልግሎት አሰጣጥ ላይ
- በGender & Assertiveness
በአጠቃላይ በ15 አይነት ስልጠናዎች 50 ሰዎችን በመስክ የሙያ ማሻሻያ ስልጠናዎችን ሲሰጥ ከደ/ብርሃን ዩንቨርስቲ ጋር በመተባበር ለ18 መምህራን /የHDP/ Higher Diploma ት/ት አሰጥቷል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ከ18 በላይ ለሆኑ ለአስተዳደር ሠራተኞችና መምህራንም የኮምፒዩተር Skill ት/ት የሰጠ በመሆኑ ኮሌጁ የሚሊኒየሙን ግብ ለማሳካት እና ራዕዩን እውን ለማድረግ ኮሌጁ ጠንክሮ እየሠራ ነው፡፡