ደብረ ብርሃን ጤና ሳይንስ ኮሌጅDebre Birhan Health Science College

ምልክቶች

የኮቪድ-19 ምልክቶች

በአብዛኛው ጊዜ የሚታዩ የኮቪድ-19 ምልክቶች፡

? ትኩሳት

? ድካም

? ደረቅ ሳል

አንዳንድ በሽተኞች ህመም ሊሰማቸው ይችላል፤ የአፍንጫ መደፈን ወይም ፈሳሽ መብዛት የጉሮሮ ህመም እና ተቅማጥ ሊኖራቸው ይችላል:: በአብዛኛው እነዚህ ምልክቶች መለስተኛ እና ቀስ በቀስ መታየት የሚጀምሩ ናቸው፤ አንዳንድ ሰዎች በበሽታው ቢያዙም እነዚህ ምልክቶችም ሆኑ የህመም ስሜት ላይሰማቸው ይችላል:: ብዙ ሰዎች (80% ያህል) የተለየ ህክምና ሳያስፈልጋቸው ከበሽታው ሊያገግሙ ይችላሉ በኮቪድ-19 ከሚያዙ ሰዎች አንድ ስድስተኛ የሚሆኑት በጠና ታመው የመተንፈስ እክል ያጋጥማቸዋል:: በእድሜ የገፉ ሰዎች እና እንደ ደም ግፊት፥ የልብ ወይም የስዃር በሽታ ተጠቂ የሆኑ ሰዎች በጠና ሊታመሙ ይችላሉ::

Source: Ministry of Health, Ethiopia